9:38
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ከስሕተት ያለመማር ውጤት እንደኾነ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ ▶️ በዐማራ ክልል፣ እስከ ስድስት ወር ተፈጻሚ እንዲኾን በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀውና ዛሬ ሰኞ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ “ካለፉት አምስት ዓመታት ስሕተቶቻችን ያለመማራችን ውጤት ነው፤” ሲሉ፣ የቀድሞው የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ተቃውሟቸውን ገለጹ። የምክር ቤቱ አባላት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን በመደገፍ እና በመቃወም ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፤ ስድስት የምክር ቤቱ አባላት ያሉበት፣ “የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መርማሪ ቦርድ”ም ሠይሟል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ። 👇 | VOA Amharic
245.2K viewsAug 14, 2023
FacebookVOA Amharic
9:33
▶ በጉዳቱ መክሊቱን ያበዛው ባለአንድ እግሩ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ዋና አሠልጣኝ የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶችን፣ ከራሱ የሕይወት ገጠመኝ እየተነሣ፣ በሥነ ምግባር እየኮተኮተና በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብቁ እያደረገ የሚገኘውን፣ ባለአንድ እግሩ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ዋና አሠልጣኝ ወይም በዘርፉ የማዕርግ አጠራር ሳቦም ከማል ቃሲምን፣ የዛሬ ጋቢና ቪኦኤ ዝግጅታችን እንግዳ አድርገነዋል፡፡ በአፍሪቃ ድንቃድንቅ መዝገብ ስሙ የሰፈረው ብቸኛው ባለአንድ እግሩ አሠልጣኝ በሚሰጠው የቴኳንዶ ሥልጠና ደስተኛ ቢኾንም፣ በብዙ የሕይወት ፈተናዎች ውስጥ እንዳለፈና እያለፈ እንደሚገኝም ይናገራል፡፡ ሳቦም ከማልን ለአካል ጉዳት የዳረገው አጋጣሚ የተፈጠረው፣ ገና የስድስት ዓመት ሕፃን እያለ በ1985 ዓ.ም. ነበር፡፡ የ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥን ያማጣው ጦርነት ቅሪት በኾነና በወረታ ከተማ በተተወ
72.8K viewsDec 22, 2023
FacebookVOA Amharic
2:49
🎙 ዜና እፍታ - ባለፈው ሳምንት የኮንጎን ትልቁን ምስራቃዊ ከተማ፣ ጎማን የተቆጣጠረው እና በሩዋንዳ የሚደገፈው የኤም 23 ታጣቂ ቡድን ወደ ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል እየገፋ መሆኑ ተገለጸ። - እስራኤል ኢራን የሲቪል ማመላለሻ አውሮፕላኖችን በመጠቀም ለአሸባሪው ሂዝቦላህ ቡድን ገንዘብ ታቀብላለች የሚል ክስ ከአቀረበች ከአንድ ቀን በኋላ፣ ሊባኖስ የኢራን ንብረት የሆነ አውሮፕላን ወደ ቤይሩት እንዳይገባ አግዳለች። - የአሜሪካ ፀረ ሽብር ቢሮ ኃላፊ እና የፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ልዩ ረዳት የሆኑት ሰባስቲያን ጎርካ፣ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ወቅታዊውን የሽብር ስጋት አስመልክቶ ግምገማ እንዳደረጉና፣ በዋናነት የሚጠቀሰውም የእስልምና አክራሪ ቡድኖች የሚገኙባቸው ሥፍራዎች እየጨመረ መምጣት ሲሆን፣ ትስስራቸው በሳህል፣ በመካከለኛውና መሥራቅ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲሁም መካከለኛው
3.7K viewsFeb 14, 2025
FacebookVOA Amharic
See more
Static thumbnail place holder